Thank you

የኢትዮጵያ ወዳጆች

ኩያቭስኮ ፖሞርስኪ ከሚባለው አውራጃ ሆስፒታል ሓኪሞችና ነርሶች በፈቃዳቸው ኢትዮጵያ በመሄድ የነጻ ሕክምና መስጠታቸውን እያስታወስን ለተደረገላቸው አቀባበልና በሥራቸው ላይ ለቀረበላቸው ታላቅ እገዛና ትብብር ለሠሩበት ሆስፒታል ተውካዮችና መሪዎች ታላቅ ምስጋናችንን አቀረብን። ቡድኑ የሠራውን ሥራ ዝርዝር ስላቀረበልን ከዚህ በታች እንገልጻለን፤

10 ኔውሮሰርጀሪ
24 ኦርቶፔዲስት
8 ቀዶ ጥገና-ሰርጂካል
59 የዓይን ኦፐሬሽን – “የኢትዮጵያ አይኖች” ፕሮጀክት

ይህ የእርዳታ ትብብር ካለው ታላቅ ችግር ሲታይ በቂ እንዳልሆነ ቢታወቅም ሃሳቡ ወደፊት እንድሚቀጥል ያለንን ተስፋ በመግለጽ በድጋሜ ምስጋናችንን አቀረብን።
ይህንን ሥራ ለመሥራት የተጠቀሙበትን እቃዎች በነጻ የለገሱን ድርጅቶች እንደሚከተሉት ናቸው፤

የፖላንድ ሰዎች፤ ለሰው ታላቅ ፍቅር ያላቸው ናቸው

በኢትዮጵያ የሚካሄደው የውስጥ ጦርነት ለሕዝቡ ያደረሰውን ጉዳት የተሰማቸው የኢትዮጵያ ወዳጅ አገር ፖላንዶች፤ ታላቅ ልምድ ያላቸው ሃኪሞችና ነርሶች በገዛ ወጪአቸው ኢትዮጵያ ሄደው የህክምና እርዳታ መስጠትና የሕክምና ጊዜአዊ እውቀቶችን ለኢትዮጵያ ዶክተሮችና ነርሶች በማካፈል አድናቆት የሞላው ሥራ ሠርትው ተመልሰውል። በኢትዮጵያና ፖላንድ ማሕበር የተሰበሰበውን ብዙ የሕክምና መሣሪያውችና መድሃኒቶች ይዘው ሄደው ለሆስፒታሎቹ ሰጥተው ተመልሰዋል። ይህ ሥራ ወደፊት በኢትዮጵያና ፖላንድ ሊኖር የሚችለውን መተባበር በር ይከፍታል ብለን እናምናለን። ታላቅ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ቀጣዩ የፖላንድ የወዳጅነት እርዳታ እጅ ለኢትዮጵያ

ከሁለት ዓመት በላይ የሚካሄደው የውስጥ ጦርነት የተለያየ አመለካከት ተሰጠበት። ለሃያ ሰባት ዓመት አገሩን ያስተዳደር የነበረው ፓርቲ የሕዝቡን እምነት በማጣቱና በፓርላመቱ አዲስ መሪ ስለተመረጠ በተለያዩ መንገዶች ስልጣን እንደገና ለማያዝ ብዙ ሙካራ አድርጓል። የፖለቲካ ፓርቲ ስልጣን ለመያዝ ሕዝቡን የሚያሳምን ለሕዝቡ የሚጠቅም ፕሮግራም በማቅረብ ሥልጣን ይረከባል እንጂ ሥልጣን ለመያዝ ጦርነት አይከፍትም፤ ወገኖቹን አይገድልም። ይህ ጦርነት ያመጣው ትርፍ ቢመረመር ብዙ ሕይወታቸውን ያጡ ወታደሮችና ገለሰቦችና በከፋ የቆሰሉ ሰዎችን ነው።

ይህ አስከፊ ጉዳት የተሰማቸው የኢትዮጵያ ወዳጅ አገር ወገኖች ታላቅ ልምድ ያላቸው ሃኪሞችና ነርሶች በገዛአ ወጪአቸው ኢትዮጵያ ሄደው የህክምና እርዳታ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ለመስጠትና የሕክምና ጊዜአዊ እውቀቶችን ለኢትዮጵያ ዶክተሮችና ነርሶች ለመስጠት ተዘጋጅተው ተነሱ። ብዙ የሕክምና መሣሪያውችና መድሃኒቶች(ለሆስፒታሎቹ ሰጥተው የሚመለሱት) አሰባስበው በቅርብ ቀን ኢትዮጵያ ለመሄድ ተዘጋጅተዋል። እነዚህ የማሕበር አባላችን ዶ/ር ብዙ አየሁ ተገኔ ያደራጃቸው ሓኪሞች፡ ሶስት ሰመመን ሰጪዎች፤ ሁለት የነርቭ ቀዶ ጥገና ሓኪሞች፤ አንድ የቀዶ ጥገና ሓኪም፤ አንድ የኦርቶፐዲክስ ሓኪም፤ አንድ የዓይን ሓኪምና አራት ባለታላቅ ልምድ ነርሶች ናቸው።

ይህ የነዚህ ሕኪሞች ውሳኔ በፖላንድ ለምንኖረው ወገኖች የሚያሳየን ትልቅ ነገር የሰው ፍቅርና አክብሮት ባላቸው ሕዝቦች ውስጥ እንደምንኖር ነው። ከዚህ በፊት እንዳስታውቅነው በዚህ ጽሁፍ ርእስ ቀጣዩያልንበት ምክንያት የኢትዮጵያ አይኖችተብሎ የሚጠራው፤ አቶ ስታኒስላቭ ኮትላርችክ በሚባለው የማሕበራችን የክብር ማሕበር አባል የሚመራው የርዳታ ሰጪ ቡድን እስክሁን ከ 3000 በላይ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን አይነ ስውሮች አይናቸው ተከፍቶ ቤተሰባቸውንና ዓለምን እያዩ እንዲኖሩ ረድቷል። ማሕበራችን የኩላሊት ችግር ላለባቸው ሁለት ወጣት ወገኖች የዲያሊዛ ሕክምና እየርዳ ነው። ይህም ታላቅ የሰው አክብሮትና ፍቅር ባላቸው ሰዎች እርዳታ ነው። በየጊዜው ማሕበሩ እንደሚያደርገው ሁሉ ባሁኑ ወቅት ብዙ የኢትዮጵያ ወጣቶች አገር ጥለው ፖላንድ እየገቡ ሲሆን ከታሰሩበት አስለቅቆ የትምህርታ የሥራ እድላቸውን እንዲሞክሩ ብዙ እየረዳ ነው።

ይህ የቀዶ ጥገና ቡድን በ11 ፌብሩዋሪ ኢትዮጵያ ይሄዳል።

በቃ

መላው ዓለም እንደሚያደርገው የፓርላመንት ምርጫ ሲታወጅ የፖሊቲካ ፓርቲዎች ለህዝቡ ይጠቅማል ብለው ያሰቡትን ፕሮግራም በማቅረብ ሕዝቡ እንዲመርጣቸ(ለሥራ እንዲቀትራቸው) ይታገላሉ። የሠለጠነው ዓለም የማያውቀው አዲስ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ታየ። ከፓርቲዎቹ አንዱ ለምርጫ ከመወዳደር ይልቅ በኃይል ሥልጣን ለመያዝ በመንግስቱ ላይ ጦርነት አወጀ። ይህ ታላቅ እልቂትና ጉዳት አደረሰ። ዘረፋ፤ አስገድዶ ህጻናትንና ሰቶችን መድፈር፤ መዝረፍና መግደል የታዩት ሰቃቅ ድርጊቶች ናቸው። ይህን ድርጊት መንግስት ዝም ብሎ አያይምና የሕግ ማስከበር ድርጊቱን ሲጀምር የውጪና የውስት ጠላቶች የኖብል ተሸላሚው ባገሩ ህዝብ ላይ ጦርነት አወጀ እያሉ መጮህ ጀመሩ።

ይህ ጨካኝ ጦርነት ያመጣውን ታላቅ ጉዳት በመገመት ማሕበራችን እንዳቅሙ እርዳታ ለማረግ ባቀደው ፕላን መሠረት፡ በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖቻችንን የሕክምና እርዳታ ለማረግ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንቆማለንበማለት 12 የሕክምና ባለሙያዎችና 3 የቡድኑ አስተባባሪዎች የተጎዱ ወግኖቻችን ባሉበት ቦታ ሄደው የቀዶ ጥገናና አስፈላጊ ሕክምና እርዳታ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። ይህን የተከበረ አላማ ከግብ ለማድረስ የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ በኢትዮፖላንድ ማህበር “SELAM” ስም በትህትና እጠይቃችኋለሁ።

እውነተኛ ምርጫ

በዚህ ዓመት የተደረገው የሕዝብ ምርጫ ለብዙ አገሮች ምሳሌ ይሆናል የሚል እምነት አለ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን አስከብሮ ክፉ የተባለውን መንግስት ከሥራ አሰናብቶ አገር ወዳጅ የሆኑትን መሪና ተወካዮች መርጦ የሥራቸውን ውጤት መጠበቅ ጀምሯል።  ዘር የለሹም የአባይ ግድብ ሁለተኛ መሞላቱን ጨርሶ የኢትዮጵያን ሕዝብ አኩርቷል።  የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላክ ይመስገን እንላለን።

አዲስ ምእራፍ

የኢትዮጵያ ሕዝብ  የብልጽግናውን መሠረት ገንቢ ሠራተኞቹን መምረጫ ጊዜው እየተቃረበ ነው። ብዙ ቃል የገቡ የተለያዩ ፓርቲ አባሎች ቃላቸውን ወደ ብልጽግና ድርጊት ሲያውሉት ለማየትም ጊዜው ተቃርቧል። የሕዝቡ ውሳኔ የመጨረሻ ነውና በርጋታ እንጠብቅ ከዛም የተቀጠሩት ሠራተኞች የሚያመጡትን ለውጥ እንይ። እግዜር  ከኢትዮጵያኖች ጋር ይሁን።  አሜን

ማሕበራችን በአዲሱ በሽታ ለተሰቃዩት ወገኖች የተደረገ እርዳታ

ETHIO – POLISH ASSOCIATION – SELAM

UTILIZATION OF FUND RECEIVED FOR THE COVID 19 SUPPORT

ETHIOPI-2020

In the name of the Missionary sisters Servants of the Holy Spirit, I extend a heartfelt gratitude to the Ethio-Polish Association- SELAM for the financial support received. The funds received were divided to three communities where the sisters are working, mainly Alemtena, Waragu and Chole. Each community selected beneficiaries who were in need of help, and food and hygiene materials were distributed to them.

Here below each community gives a short account of their intervention, followed by the financial report.

Waragu community

The people who are most affected here in Waragu are the daily workers, farmers, petty traders and the elderly whose life mostly depends on the mercy of others. They earn their living on daily basis. In Waragu village the people depend mostly on traditional agriculture for their livelihood. The area is very fertile but drastic changes of weather and persisting drought do not allow them to harvest a good return. Therefore people in this area remain poor.

With the financial support received from the ETHIO – POLISH ASSOCIATION – SELAM, we were able to give food support to 80 families, with 1- to 9 children per household. Each of these families received – Teff, Corn, beans powder/Shiro, oil and soap for personal hygiene.

The beneficiaries were chosen with the help of the local administration. The beneficiaries were from the five nearby villages. Namely: Waragu, Derole, Haro, Kela and Ibdo .

In order to support the petty traders, the food stuff was purchased from the local market. The beneficiaries and people were extremely grateful to the benefactor, the Ethio-Polish association SELAM, for the great help rendered to the people during this pandemic. May God bless your generosity.

Alemtena Community

COVID-19 has made the humanity all over feel helpless. In this time of struggle and cry of the poor, God sends His messengers through various ways to uplift the poor and the hungry by their generosity and compassion towards the people. As people in Ethiopia were getting ready to celebrate their New Year on September 11, 2020 (Meskerem 01, 2013), we have received the good news that Ethio – Polish association SELAM was extending a generous donation to help the poor in our area.

With the amount given to our community, we budgeted to provide food stuff for 100 families and to make four pedal wash stands for the hand washing for everyone who enters the compound. In the town of Alemtena there were University students who had volunteered for social service during this time of COVID-19 lock down. Twelve students visited the poor families and brought the list of the deserving families to us. We had also included the families of orphans and vulnerable children studying in our school in Alemtena.

They were called in three different groups and following items were distributed: Teff, rice, Shiro, Chili powder, salt, oil and soap for their hygienic needs.

As the Alemtena Catholic Church Clinic continued to reach out to the patients during the pandemic, three medical staff members tested positive with COVID. All staff of the clinic, including the sisters community and some teachers who were in contact with the people infected were ordered to go into quarantine. Since they had no possibility to isolate themselves at home, the quarantine was arranged in the mission compound itself. Medication of the staff members and providing food for all those in quarantine were also part of the donation expense.

The beneficiaries were explained about the donor, the SELAM Association. And they were given education on COVID-19, how to protect themselves and others, and how they were to increase their immunity. The people thanked the SELAM Association for their generosity and compassion.

We, the Alemtena community of sisters, express our sincere thanks to ETHIO- POLISH Association SELAM for giving us the opportunity to reach out to our people with the support they needed during this difficult time.

May God bless you and protect you.

Chole Community

COVID 19 has affected economically very much our people here in Chole, a small town around 225 km from Addis Ababa. Everyone around is affected in one or the other way by this pandemic. But the people who are most affected by it are daily workers, who earn their income with daily labor like the ones working in hotels, the youth and children who are doing shoe polishing, domestic workers and the elderly who are living at the mercy of others.

Chole town harbors around 30,000 people and with the financial support that we have received from you, we were able to give food support to 75 registered families, with 1- to 7 children per household.

Each of these families received – Teff (local grain to prepare the staple food of Ethiopia), oil, wheat flour, Shiro ( Flour made out of beans) and salt.

The animators delivered the food stuff at home to those who were not able to come to the compound. Prior to the distribution, we discussed the matter with the district administrator, they were grateful that we could extend our helping hand towards the most vulnerable people who are the victims of COVID 19.

The district administrator and the staff helped us in choosing the beneficiaries; the staff of the Family development project (run by the sisters) visited the houses of these beneficiaries to assess the condition in which they are living and to see how this pandemic has really affected them.

In order to alleviate at least little bit of their hunger we bought food stuff which was distributed to these beneficiaries in the presence of the District administrator Kanjawe Danja, his assistant Joseph Tola, Representative from women and youth office Mr. Nowai Zaid and the chair person of social emergency department Miss. Membere Meseret. The beneficiaries and the government officials were extremely grateful to the Sisters who with the support of the Ethiop-Polish Association Selam extended help to the people during this pandemic.

We, the sisters working in Chole, express our gratitude to all who have contributed to this act of reaching out beyond boarders to those in need. God bless you all…

We, the Missionary Sisters Servants of the Holy Spirit, extend our heart gratitude to you, Ethio-Polish Association-SELEM for your generous sharing of your finance with the people of Ethiopia. Thank you very much. God bless each one of you.

እግዚአብሔር ከኢትዮጵያኖች ጋር ይሁን

በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ጦርነት ሃቀኛውን የትግሬ ሕዝብ እንዳይጎዳ የሚል ስጋት አለብን። መንግሥቱ ሰላአማዊውን የትግሬን ሕዝብ ላለምጉዳት የተቻለውን ሁሉ እናደርጋለን ያለውን የዶ/ር አብይ መንግስታዊ የጦር ኃይል ቃል በእምነት ወስደነዋል።

 

አሰቃቂው መሪ

ሰሞኑን የሰማነው፤ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፤ የተናገረው ንግግር በጣም የሚያሳዝን ነው። እንዴት አንድ የታላቅ አገር መሪ እናስማማችሁ ሲል ቆይቶ ሁለት አገሮች ጦርነት እንዲከፍቱ ይጠራል ? ይህ ሰው የሚመራቸው ሕዝቦች ምን ያህል ያፍሩ ይሆን ? ታዲያ ይህ ሰው ይህን አይነት ታላቅ አገር መምራት ይችላል ወይ የሚል ጥያቄም በሌሎች ዓለም አቀፍ ሕዝቦች እንደታሰበ መገመት አያስቸግርም። የዓለም መሪዎች ብዙ አነጋጋሪ ዜናዎችን አሰምተዋል ግን ሕዝቦችን ከማስማማት ይልቅ ሁለት አገሮች ጦርነት እንዲከፍቱ ጥሪ ማድረግ እስካሁን ተሰምቶም አያውቅም። ታዲያ ይህን እርምጃ እንዴት እንተርጉመው ? ፕሬዚደንቱ ከግብጽ ጎን ያቆመው ምክንያትስ ምንድነው ? የአብይ ወንዝ በገደቡ ምክንያት ወደ ሱዳንና ግብጽ መፍሰሱ እንዳልቆመ ፕሬዚደንት ትረምፕ የሚያውቅ አይመስልም። ያሳዝናል። ሌላ በሃሳብ የሚመጣው መልስ፤ ፕረዚደንቱ አሜሪካንና መላውን ዓለም እንደራሱ የግል ድርጅት እያሰበ ይሆን ? አሁን ይደግፏት የነበሩት መራጭ የአሜሪካ ሰዎች ምን ምርጫ ቀራቸው ? ወይስ ሆነ ተብሎ ፤ ምርጫውን እንዲሸነፍ ባማካሪዎቹ የታቀደ ሴራ ይሆን ? ወደፊት የምናየው ታሪክ ይሆናል።