እንቅስቃሴአችን

የኢትዮጵያና  ፖላንድ ማኅበር  „ሰላም”  በፖላንድ  የሚኖሩትን  ኢትዮጵያውያን ፤  የፖላንድ  ዜግነት  ያላቸውን  ኢትዮጵያውያንና  የማኅበሩ  አባል  የሆኑትን  የፖላንድ  ዜጎች  ለመወከል  በኅግ  የተመሰረተ  ማኅበር ነው።  ዋናዎቹ እንቅስቃሴዎች ፤
•    በትምህርትና  እውቀት፤ በኅብረተሰብ ፤ በባህልና በስፖርት በኩል ለሚደረጉ እንቅስቃሴውች  የሚቻለውን ትብብር እርዳታና ማበረታቻ  መስጠት፤
•    የማኅበሩ አባላት  ግላዊና  በስራቸው በሚያረጉት እንቅስቃሴዎች  ኅጋዊ  ድጋፍ  መስጠት
•    ከላይ የተጠቀሱትን  እንቅስቃሴዎች  ለማሳካት  እንዲችሉ  የተለያዩ  ስብሰባዎችና  ሴሚናሮች  ማዘጋጀት
•    አባላት  ለሚያደርጉት  እቅድ  ሊረዳ  የሚችል  ገንዘብ  ማግኛ  ጥረቶችን  ማድረግ  ከሚጠበቅበት  ሥራዎቹ  ጥቂቶቹ  ናቸው።
የማኅበሩ  አባላት  ከማኅበራችን  ጋር  የቅርብ  ግኑኝነት ያላቸው ማኅበሮች፤ ድርጅቶችና  ግላዊ  ኅብረሰቦች   በሃሳብና  በግብር  ለሚያደርጉት  እርዳታ  ታላቅ  ምስጋናቸውን  ያቀርባሉ።
የኢትዮጵያና  ፖላንድ ማኅበር  „ሰላም”  ከኢትዮጵያ ድርጅቶችና  ማኅበሮች  ጋር  የትብብር  ሥራ  ለመስራት  ፍላጎት  ያላቸውን  ድርጅቶችና  ግላዊ  ሰዎች  እቅዳቸውን  ለማስፈጸም  የሚያደርጉትን  ጥረት   በሰፊው  በመደገፍ  የሚቻለውን ሁሉ  ለመርዳት  ዝግጁ መሆኑን  ይገልጻል።  ወደ  ኢትዮጵያ  በመሄድ  እቅዳቸውን  ለማስፈጸም  ይረዳ  ዘንድ  አስፈላጊ ከሆነም   የማኅበራችን  አባል  በአስተርጉዋሚነት ሊተባበራቸው  እንደሚችል  በዚሁ  አጋጣሚ  እንገልጻለን።
ኢትዮጵያን  ለመጎብኘትም  ሆነ  ለአደን  መሄድ  ለሚፈልጉም  ተመሳሳይ  እርዳታችን  እንደማይለያቸው  በዚሁ  አጋጣሚ  እንገልጻለን።
የኢትዮጵያና  ፖላንድ ማኅበር  „ሰላም”  ከማንም  የፖለቲካና  አስተዳደር ተጽእኖ  ነጻ  የሆነ  ማኅበር  ሲሆን  ኢትዮጵያን  በሚመለክት  በርሊን  ከሚገኘው  የኢትዮጵያ  ኢምባሲ  ጋር  የቅርብ  የስራ ትብብር  ያደርጋል።