2930 ኢትዮጵያኖች ከጨለማ ወደ ብርሃን ገቡ።

ብዙ ባልተነገረለት ባልታወጀለት ኢትዮጵያን ወዳዶች የፖላንድ ሰዎች ሰብዓዊ “የኢትዮጵያ ዓይኖች” የሚባለው ሥራ በነፃ ኦፐሬሽን በመደረግ ከጨለማ ወጡ። በኢትዮጵያና ፖላንድ ማሕበር “ሰላም” የታቀፈው ይህ ቡድን 11 ጊዜ በግል ወጪአቸውና ይህ ቅዱስ ሥራ መንፈሳቸውን የነካቸው ሰው ወዳድ ሰዎች ባደረጉት እርዳታ ኢትዮጵያ እየሀዱ በለፃ 2390 ቀዶ ጥገና እና የዓይን መርመራ በማድረግና 1500 መነጽር በነፃ በመስጠት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅራቸውን አስመስክረዋል። እናመሰግናለን። ይህ የአይን መክፈት ሥራ ቁጥር በቂ ገንዘብ ብናገኝ ኖሮ የበለጠ ሊሆን በቻለ ነበር። ይህ ቅዱስ ሰብዓዊ ሥራ እንዴት ተጀመረ ? የቡድኑ መሪ ስታኒስላቭ ኮትላርችክ የተባለው የማህበራችን ወዳጅ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ላሊበላ በሄደብት ጊዜ አንዲት አይን ስውር ሴት በትንሽ ልጇ እየተመራች ስትሄድ ያያል። ልቡ ስለተነካ በገዛ ወጪው አዲስ አበባ ባውሮፕላን ልኮ በገዛ ወጪው ኦፐሬሽን እንድትደረግ ይወስናል። ይህ በጭለማ መኖር ችግር በዚች ሴት ብቻ ያልሆነና ብዙ ለመታከም አቅማቸው የማይፈቅድላቸው ሰዎች እንዳሉ ሲገነዘብ ፖላንድ ከተመለሰ በኋል “የኢትዮጵያ ዓይኖች” የተባለውን ለበጎ ሥራ የቆመ አሠራር ይመሰርታል። ስታኒስላቭ በተረዱት የኢትዮጵያ ሰዎች ስም በጣም እናመሰግናለን። ሌላው ምስጋናችን ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ቅዱስ ሥራ ለሚሰሩት የቡድን አባላት እርዳታ ለሚያረጉት ኢትዮጵያን ወገኖቻችን ይሆናል።የኢትዮጵያ ዓይኖች” አባሎች በተጨማሪ ለ20 የኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚያረጉት ቋሚ እርዳታ ልባችንን የነካው ነው። ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት መላክ የማይችሉ ወላጆች በዚህ እርዳታ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ነው። እናመሰግናለን !!