ሰላም 2018

የማሕበራችን ዓመታዊ ስብሰባ ደስ በሚል ስሜት ዶምቤ በሚባለው ቦታ ሃይቅ አጠገብ አሳለፍን። በተለይ በኢትዮጵያ አገራችን የሚካሄደውን ታላቅ ለውጥ በልባችን ይዘን ተደስተን አሳልፈናል። ስብሰባውን ባስደሳች ሁኔታ ያዘጋጁልንን ቴማር የተባለው ድርጅት ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከልብ እናመሰግናለን። የወረዳው ገዢ የሆኑት ወ/ሮ ክርስቲና ብርሼቭስካ እንኳን ደህና መጥችሁ በማለት ተቀብለውናል። የማሕበራችን የዘመን ረጂና ጓደኛ የሆነችው ወ/ሮ አንና ሚኮዋይችክ የክሮስኖ ኦድዣንስኪ ከተማ አስተዳዳሪን ወክላ አብራን ተሳትፋለች፤ በጣም እናመሰግናለን። በያመቱ የገንዘብ እርዳታ የሚያረጉት የኢትዮጵያ ሆኖረብል ኮንሱል ዶ/ር ሮማን ሮየክ ላደረጉልን እርዳታ በዚህ አጋጣሚ ልናመሰግን እንወዳለን።