2930 ኢትዮጵያኖች ከጨለማ ወደ ብርሃን ገቡ።

ብዙ ባልተነገረለት ባልታወጀለት ኢትዮጵያን ወዳዶች የፖላንድ ሰዎች ሰብዓዊ “የኢትዮጵያ ዓይኖች” የሚባለው ሥራ በነፃ ኦፐሬሽን በመደረግ ከጨለማ ወጡ። በኢትዮጵያና ፖላንድ ማሕበር “ሰላም” የታቀፈው ይህ ቡድን 11 ጊዜ በግል ወጪአቸውና ይህ ቅዱስ ሥራ መንፈሳቸውን የነካቸው ሰው ወዳድ ሰዎች ባደረጉት እርዳታ ኢትዮጵያ እየሀዱ በለፃ 2390 ቀዶ ጥገና እና የዓይን መርመራ በማድረግና 1500 መነጽር በነፃ በመስጠት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅራቸውን አስመስክረዋል። እናመሰግናለን። ይህ የአይን መክፈት ሥራ ቁጥር በቂ ገንዘብ ብናገኝ ኖሮ የበለጠ ሊሆን በቻለ ነበር። ይህ ቅዱስ ሰብዓዊ ሥራ እንዴት ተጀመረ ? የቡድኑ መሪ ስታኒስላቭ ኮትላርችክ የተባለው የማህበራችን ወዳጅ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ላሊበላ በሄደብት ጊዜ አንዲት አይን ስውር ሴት በትንሽ ልጇ እየተመራች ስትሄድ ያያል። ልቡ ስለተነካ በገዛ ወጪው አዲስ አበባ ባውሮፕላን ልኮ በገዛ ወጪው ኦፐሬሽን እንድትደረግ ይወስናል። ይህ በጭለማ መኖር ችግር በዚች ሴት ብቻ ያልሆነና ብዙ ለመታከም አቅማቸው የማይፈቅድላቸው ሰዎች እንዳሉ ሲገነዘብ ፖላንድ ከተመለሰ በኋል “የኢትዮጵያ ዓይኖች” የተባለውን ለበጎ ሥራ የቆመ አሠራር ይመሰርታል። ስታኒስላቭ በተረዱት የኢትዮጵያ ሰዎች ስም በጣም እናመሰግናለን። ሌላው ምስጋናችን ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ቅዱስ ሥራ ለሚሰሩት የቡድን አባላት እርዳታ ለሚያረጉት ኢትዮጵያን ወገኖቻችን ይሆናል።የኢትዮጵያ ዓይኖች” አባሎች በተጨማሪ ለ20 የኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚያረጉት ቋሚ እርዳታ ልባችንን የነካው ነው። ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት መላክ የማይችሉ ወላጆች በዚህ እርዳታ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ነው። እናመሰግናለን !!

100 ዓመት ነፃነት በዓል

የፖላንድ ሕዝብ የ 100 ዓመት ነፃነት በዓሉን ያከብራል።  እንኳን አደረሳችሁ እንላለን። በነፃነት ወደፊትም እንድትደሰቱ እነመኛለን።

ስጋታችን

ብስሉ የኢትዮጵያ መሪ ዶ/ር አብይ አህመድ አውሮፓ ወገኖቹን ለማግኝት ሊመጣ ነው። በደስታ እንቀበለው፤ ስጋታችንንም እንንገረው። የሰላምና የደስታ ጊዜ ያርግልን። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የቀድሞው ስር ዓት መሪዎች በዘረፉት ኃብት ሕዝቡን ሲያጋድሉ “ተዉ መገዳደል አያዋጣም እንደመር እንዋደድ” ከማለት ይቅር ጨካኞቹን በቁጥጥር ስል አውሎ ለፍርድ ካላቀረበ የህዝቡ ተስፋ ወደስጋት እንደሚሄድ ጥርጣሬ በዝቷል። እነሱ ከማንም አይደመሩም ከሕዝቡ ኃብት ብቻ እንጂ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ጀርመን ሊመጣ ነው

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ያውሮፓ ወገኖቹን ለማግኘት አውሮፓ ሊመጣ ነው። በኦክቶበር 31 ከቀኑ 13 ሰዓት ላይ ፍራንክፈርት ሜይን በሚባለው ከተማ ታላቅ ስብሰባ ይደረጋል። አድራሻው በ Commerzbank Arena, Morfelr Landstrasse 362, 60582, Frankfurt am Main ነው።  ይህን ታላቅ ዝግጅት መሳተፍ ለሚፈልጉ ወገኖችና ዘመዶች ታላቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ባንድነት በነፃንትና ብልፅግና ለምስተዳደር የተነሳችሁ የዶ/ር አብይ ቡድኖች !

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ

ከዚህ በፊት ያልታየ፤ ያልተሰማ ታላቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ መመጠን የማይቻል ክብደትና ጭንቀት እንደሚሰማዎት መገምት እችላለሁ። ለጭንቀቱ ሳይሆን ለሕዝቡ ድጋፉና ፍቅሩ እንኳን ደስ አለዎት እላለሁ። ታማኝ በየነ ጎንበስ ብለው እግር ለመሳም ያደረጉት ሙከራ ሃሳብዎንና ለሕዝቡ ያሳዩትን ፍቅርና ኢትዮጵያን እግር ለመሳም እንደነበር ይገባኛል። ግን ይህን ሁኔታ አይቼ እንባዬ ሲመጣ ቶሎ ብዬ ፍርሃት አኮማተረኝ። በዓለም ላይ እንደዚህ ተከብረው በስልጣን መርዝ አውሬ የሆኑ መሪዎች ትዝ አሉኝ። ስልጣንና ገንዘብ መርዝ ናቸው። ያልገዙት ያልለወጡት የሰው ተፈጥሮ የለም። ዉሾች ጠግበው የኢትዮጵያ ህዝብ በረሃብ የሞተበት ስርዓት ሲቀየርና አንጀቱን በገመድ እያሰረ “አገሬ ኢትዮጵያ” ሲል የነበረው ደርግ በመጀመሪያ ህዝቡ እልል ብሎለት ነበር። የንጉሱን ባለስላጥናት እንደበግ አስሮ በሕግ ፊት ሳያቀርብ መረሸኑ “ከሕግ በላይ” መሆኑን ሲያሳይ ነበር ኢትዮጵያ መከራ እንደገባች የገመትነው። ሕግ የማይከበርበት ስርዓት ምን ጊዜም ቢሆን ሰላም አያመጣም።
ዘራፊዎቹ፡ ገዳዮቹ፤ ጨቋኞቹ እንደፈለጉት ሲዝናኑ አንዳንዶቹም ሲሾሙ አገራችን ውስጥ ሰላም አይመጣም።
ፖላንድ በ”ሶሊዳርኖሽች” በሚባለው የትግል መመሪያ የኮሙኒስቱን ስርዓት ከስልጣን ሲያገሉ መጀመሪያ የተመረጠው ጠ/ይ ሚኒስቴር ወፍራም ስረዝ በሚል የይቅርታ ቃል በመግባት በሩሲያ እየተመራ ህዝቡን ሲጨቁን የነበረውን ፓርቲ አባሎች ዝም ብለው ያለጥያቄ ለቀቋቸው። ከላይኛው ስልጣን ዞር ብለው ከስር ያለውን ያስተዳደር ኔትዎርክ የፍርድና የደህንነት ክፍልን ይዘው ህዝቡን ሲያባሉትና ሲበዘብዙት ኖሩ ። የሚያሳዝነው ግን የመጀመሪያው የሶሊዳሪቲ መሪ በሕዝብ የተመረጠው ፕሬዚደንት ቀጥሎም የኖብል ሽልማት የተሰጠው ሰው የኮሙኒስቶቹ ድብቅ ሰላይ መሆኑ ሲገለፅ ነበር። ይህ ነው የ”ይቅርታ” ትልቁ ስህተት። እኔ የፈራሁት ይህ ሁሉ ሕዝባችንን በተስፋ ያሰከረው ምኞት በወሬ እንዳይቀርና ሌላ ያልታሰበ የብሔር መጫረስ እንዳያመጣ ነው።
ይህንን የምጽፈው ላገሬ ያለኝ ፍቅርና ስጋት ሰላም ስላልሰጠኝ ነው።
በፖላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያና ፖላንድ ማሕበር በ2003/ም ሲመሰረት ሁሉም ብሔረሰብ ያለበት ኤርትራውያንም የሚሳተፉበት ፖሊቲካ፤ ኃይማኖትና ዘር/ብሔር ሳይል እስከዛሬ ድረስ ተግባብተን ተደምረን ኖረናል። በስርዓቱ አስቀያሚነት ምክንያት ከማንም የፖሊቲካ ፓርቲዎች ሳንጨማመር ተግባብተን ቆይተናል። ከመንግስት ተወካይ ኢምባሲዎች ርቀናል። አሁን ይህ መስሪያ ቤት በደንብ ከፀዳ ብኋላ አብሮ ለመስራት ሙሉ ፈቃደኞች ነን።
ሁሉም እንደሚሉት አምላክ/አላህ ለኢትዮጵያ ምህረቱን አቅርቦላታል አገርና ሕዝብ ወዳጅ መሪም ሰጥቷታል። የተመሰገነ ይሁን። ቀጥሎም ሳይረሳን መሪአችንን ከክፉዎች ይጠብቅልን። አሜን !!

ሰላም 2018

የማሕበራችን ዓመታዊ ስብሰባ ደስ በሚል ስሜት ዶምቤ በሚባለው ቦታ ሃይቅ አጠገብ አሳለፍን። በተለይ በኢትዮጵያ አገራችን የሚካሄደውን ታላቅ ለውጥ በልባችን ይዘን ተደስተን አሳልፈናል። ስብሰባውን ባስደሳች ሁኔታ ያዘጋጁልንን ቴማር የተባለው ድርጅት ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከልብ እናመሰግናለን። የወረዳው ገዢ የሆኑት ወ/ሮ ክርስቲና ብርሼቭስካ እንኳን ደህና መጥችሁ በማለት ተቀብለውናል። የማሕበራችን የዘመን ረጂና ጓደኛ የሆነችው ወ/ሮ አንና ሚኮዋይችክ የክሮስኖ ኦድዣንስኪ ከተማ አስተዳዳሪን ወክላ አብራን ተሳትፋለች፤ በጣም እናመሰግናለን። በያመቱ የገንዘብ እርዳታ የሚያረጉት የኢትዮጵያ ሆኖረብል ኮንሱል ዶ/ር ሮማን ሮየክ ላደረጉልን እርዳታ በዚህ አጋጣሚ ልናመሰግን እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት

በፖላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያና ፖላንድ ማኅበር ‘ሰላም’ ምን ጊዜም ቢሆን በሁለቱ አገሮች የፖሊቲካ አሰራር ጣልቃ ገብቶ አያውቅም፤ ሃሳብም ትችትም አያደርግም። የማኅበሩ አባሎች የምንሰጋው ለኅዝቦቹ ብልጽግና፤ ደህንነትና አንድነት እኩልነት ነው።   በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሜዲያ የምንሰማውና የምናየው ለሰባዓዊ ደህንነትና ዲሞክራሲ ጥያቄ ህዝቡ በሚአያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ በነዚህ ሰዎች ላይ የሚደረገው ጭቆና እስራትና ግድያ የሚያሳዝን ነው።

የኢትዮጵያ ኅዝብ እድሜውን ሁሉ በነጻነት፤ በመከባብርና በፍቅር የኖረ ኅዝብ ነው።  ህዝብን በመጨቆን፣ በማሰቃየት፤ በመግደል ያስተዳደሩ መንግስታት እድሜ እንደለላቸው ታሪክ አሳይቶናል፣ ከዚህም መማር መቻል ይኖርብናል።

በመጨረሻ፤

  • አንድነት ለየኢትዮጵያ ኅዝብ እንላለን !
  • በፖለቲካ ምክንያት በህዝብ ላይ የሚደረገው እስራትና ጭቆና ይቁም እንላለን !
  • ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ ጥያቄ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡትን በገዛ ወጎኖቻቸው ማስገደል ይቁም እንላለን !
  • ለሺ አመታት በአንድነት በመከባበር የኖረው የኢትዮጵያ ብሄር አባሎች መጨቆን ይቁም እንላለን !
  • ኢትዮጵያ ለዓለም የእድገት ምሳሌ መሆን እንደምትችል እያሳየች በብሄር አለመከባበር ሰላም ማጣቷ ይቁም እንላለን!
  • ማንኛውም ብሄር ከማንኛውም አይበልጥምና በህዝብ ቁጥር ሳይሆን በዉክልና እኩልነትን የሚያስከብር ስርአት ይፈጠር ይከበር እንላለን!
  • የግል ጥቅምን ብቻ ሳይሆን የህዝብን ደህንነትና ብልጽግና ላይ የሚያተኩር ስርዓት ይፈጠር እንላለን!

 

አምላክ ከኢትዮጵያ ኅዝብ ጋር ይሁን

የፖላንድና ኢትዮጵያ ማህበር „ሰላም” አባሎች

ፖላንድ